በኢቢቪ ዘጋቢ
የቡና አምራቾችና አቅራቢዎች በእጃቸው ያለውን የቡና ምርት በፍጥነት ወደ ገበያ ሊያቀርቡ እንደሚገባ ተጠቁሟል
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) ባለፉት ሁለት ወራት የቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እየቀነሰ መምጣቱን ተናግረዋል።
ቡና በተመረተበት ዓመት ለገበያ መቅረብ እንዳለበት በህግ የተቀመጠ ቢሆንም ዋጋ ይጨምራል በሚል ምርት ይዘው የተቀመጡ ላኪዎች እንዳሉ ጠቁመው ለአንድ ዓመት ያህል የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በዚሁ ሊቀጥል እንደሚችል ተገንዝበው በእጃቸው ያለውን ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሀገራዊ የኮንትሮባንድ ንግድን የሚከላከል ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውሰው በኮንትሮባንድ ለመላክ ጥረት የሚያደርጉ አካላት ላይ ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ከቡና ወጪ ንግድ ገቢ መገኘቱን ጠቁመው በዘንድሮ በጀት ዓመትም 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከ2ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ቡናን ለዓለም አቀፍ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ የላኪነት ፈቃድ ማግኘታቸውን ጠቁመው፤ 500 ያህሉ ቀጥታ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።@SECO


