የባንኮች ፍላጎት ለጨረታ ከቀረበው የውጭ ምንዛሬ በሁለት እጥፍ ተኩል የላቀ ሆኗል
የትይዩ ገበያ ዋጋ እየተዳከመ ነው ቢሆንም የባንኮች የውጭ ምንዛሬ የመግዛት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡
ዛሬ በተደረገው መደበኛ ጨረታ የብሄራዊ ባንክ 70 ሚሊየን ዶላር ለመሸጥ ያወጣ ቢሆንም የተሳተፉት 30 ባንኮች በጥቅሉ 241.5 ሚሊየን ዶላር ለመግዛት መፈለጋቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪ አንድን ዶላር ለመግዛት የቀረበው የብር መጠን 158.5 ብር ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ጨረታ የ2.5 ብር ወይም የ1.6 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነው፡፡
አማካኝ ጨረታውን ያሸነፈው ዋጋ 157.46 ብር ለአንድ ዶላር ሲሆን ይህም ከሁለት ሳምንት በፊት ከተደረገው ጨረታ አንፃር የአንድ በመቶ የብር መዳከም የታየበት ነው፡፡
በጨረታው 9 ባንኮች የቀረበውን የውጭ ምንዛሬ ተከፋፍለዋል፡፡ ይህም ለአንድ ባንክ በአማካኝ 7.7 ሚሊየን ዶላር ገደማ ደርሶታል ማለት ነው፡፡
ከባህረሰላጤው ግጭት ጋር ይሁን አይሁን ባልተወቀ መልኩ የጥቁር ገበያ ከሰሞኑ መቀዛቀዝ እያሳየ ነው፡፡ በተመሳሳይ ብሄራዊ ባንክ ጠንካራ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑ ይታወሳል፡፡@SECO


