ሚንግ ያንግ ስማርት ኢነርጂ በኢትዮጵያ 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ሊያደርግ ነው

በኢቢቪ ዘጋቢ

ሚንግ ያንግ ስማርት ኢነርጂ በኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ የ10 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ኢንቨስትመንት ሊያካሂድ ነው

በአራተኛው “ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ 2026” ከፍተኛ የንግድ ፎረም ላይ ኢትዮጵያ ከሰባት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በአጠቃላይ ከ13.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚገመት የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርማለች።

ከእነዚህም መካከል ግዙፉን ድርሻ የያዘው የቻይናው ሚንግ ያንግ ስማርት ኢነርጂ (Ming Yang Smart Energy Group Limited) ነው።

የታዳሽ ኃይል እና የኢነርጂ ዘርፍ ስምምነቶች

ሚንግ ያንግ ስማርት ኢነርጂ በታዳሽ ኃይል፣ በሃይድሮጂን መሰረተ ልማት እና በግሪን አሞኒያ ምርት ዘርፎች ላይ ትልቅ የኢነርጂ ተቋም ለመገንባት አቅዷል። 

ለዚህም ከ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚገመት እጅግ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል መድቧል።

በተጨማሪም በታዳሽ ኃይል ዘርፍ፦

👉 ጎበዝ ኤሌክትሪክ ማኑፋክቸሪንግ፦ የሶላር ሴል (Solar cell) ማምረት አቅሙን ለማስፋፋት የ150 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ለማድረግ ተስማምቷል።

 👉 ሰን ኪንግ (Sun King)፦ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ውጭ የሆኑ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ሲስተሞችን ለቤቶችና ለንግድ ተቋማት ለማድረስ የ150 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እስከ 2030 ድረስ ለማከናወን አቅዷል።

የኢንዱስትሪ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ

በዚህ ዘርፍ ግሎባል ፊውቸር ኢንቨስትመንት የ2 ቢሊዮን ዶላር ከፍተኛ ካፒታል በመመደብ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና ለማቋቋም ስምምነት አድርጓል። 

ሊያኦኒንግ ፋንግዳ ግሩፕ በበኩሉ የብረት እና የመድኃኒት ማምረቻ ፋብሪካዎችን ለመገንባት የ500 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ራሽሚ ግሩፕ (Rashmi Group) በኢትዮጵያ ወርቅ፣ ሊቲየም እና ሌሎች ብርቅዬ ማዕድናትን ለማፈላለግ እና ለማውጣት የ235 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ተጠቅሞ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጿል። 

በሪል እስቴት እና ንግድ ዘርፍ ደግሞ ኳንተም-ኤቨረስት ከፖላንድ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ኢንቨስትመንቶችን ለማመቻቸት እና በልማት ስራዎች ለመሰማራት የ100 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል መድቧል።

ይህ በአራተኛው ዙር ፎረም የተመዘገበው የ13.1 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያፋጥነው ይጠበቃል።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories