በባሕረ ሰላጤ ጦርነት ምክንያት በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ማቅረብ እንዳልተቻ መንግስት አስታወቀ

መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ይፋ አደረገ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)  የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን የሚከታተል፣ እርምጃ የሚወስድና የነዳጅ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፍች የሚለይ ልዩ ክፍል መቋቋሙንም አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ እያካሄዱት ባለው ጦርነት  በኢትዮጵያ  የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ተጽዕኖውን አሳድሯል፡፡

ለኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የነዳጅ አቅራቢ አገራት በጦርነቱ ምክንያት ምርቱን ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን ተከትሎ በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ማቅረብ እንዳልተቻለ አስታውቀዋል፡፡

በጦርነቱና አለመረጋጋቱ ምክንያትም በነጭ ናፍጣ ላይ የነበረው የቀን አቅርቦት ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4 ነጥብብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለቱን አውስተዋል።

የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከት መንግስት እስካሁን 262 ቢሊዮን ብር ገደማ ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ያጋጠመው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በሀገርና በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንዳያሳድርና በፍትሐዊነት ለመምራት  ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቅድሚያ አሰጣጥ ውሳኔ መተላለፉን አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት

 1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው

2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ ፣

3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣

4.  የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች

5. ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች፣

6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች

7. እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ  የሚያደርግ የቅድሚያ  የነዳጅ አጠቃቀም አሠራር  የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ውጭ የሚደረግ የነዳጅ ስርጭት ተገቢ እንዳልሆነና እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories