ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢትዮጵያን በመቅደም ከሰሃራ በታች አፍሪካ 5ኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ልትሆን ነው

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እ.ኤ.አ. በ2026 የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ደረጃ በመቅደም ከሰሃራ በታች አፍሪካ አገራት መካከል አምስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ እንደምትሆን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ትንበያን ዋቢ በማድረግ ብሉምበርግ ዘግቧል።

እንደ አይ ኤም ኤፍ ግምት፣ የኮንጎ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) በዚህ ዓመት 123 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህም ኢትዮጵያ ታስመዘግባለች ተብሎ ከሚጠበቀው 122 ቢሊዮን ዶላር በትንሹ ብልጫ አለው። ለዚህ የደረጃ ለውጥ ዋነኛው ምክንያት የኢትዮጵያ ብር ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱ ሲሆን፣ በተቃራኒው የኮንጎ ገንዘብ ጥንካሬ ማሳየቱ ነው።

ኮንጎ ለዚህ ስኬት የበቃችው በማዕድን ዘርፍ፣ በተለይም የባትሪ ማምረቻ ግብዓት የሆኑት ኮባልትና መዳብ ላይ ባገኘችው ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ነው።

በተጨማሪም የኮንጎ ገንዘብ ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ባለፈው አንድ ዓመት የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በ2024 የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን ማድረጓ ለብር ዋጋ መውረድ አንዱ ምክንያት ሆኗል።

ምንም እንኳ በጠቅላላ የኢኮኖሚ መጠን ኮንጎ ብትቀድምም፣ የኢኮኖሚ እድገት ፍጥነትን በተመለከተ ግን ኢትዮጵያ በ9.2 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ከኮንጎ (5.9 በመቶ) እንደምትበልጥ አይ ኤም ኤፍ ገምቷል። በደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አንጎላ እና ኬንያ አሁንም ቀዳሚዎቹን አራት የኢኮኖሚ ደረጃዎች ይዘው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories