በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ከ12 በላይ አገራት የብድር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋና በአቅርቦት ሰንሰለት ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና ምክንያት፣ ከ12 በላይ የሚሆኑ አገራት አዲስ የብድር ድጋፍ ለመጠየቅ መገደዳቸውን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ አስታወቁ።

ዋና ዳይሬክተሯ በዋሽንግተን ዲሲ በሰጡት መግለጫ፣ በተለይም የሰሃራ በታች የአፍሪካ አገራት ለዚህ ቀውስ ማስታገሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ እየፈለጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ድርጅቱ ግምት፣ ጦርነቱ ያስከተለውን የኢኮኖሚ ድንጋጤ ለመቋቋም ከ20 ቢሊዮን እስከ 50 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ የፋይናንስ ፍላጎት ሊኖር እንደሚችል የተገመተ ሲሆን፣ ይህም አዳዲስ የብድር ፕሮግራሞችን መቅረጽን ወይም ነባር የብድር ስምምነቶችን ማሳደግን ሊያካትት ይችላል።

በተለይ የሆርሙዝ የንግድ መስመር መስተጓጎል በዓለም አቀፍ የንግድ ፍሰት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አሳሳቢ መሆኑን የገለጹት ጆርጂየቫ፣ ጦርነቱ በአፋጣኝ ቢቆም እንኳ የነዳጅና የጋዝ አቅርቦት ስርጭት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ አስገንዝበዋል።

በዚህም ምክንያት የ2026 የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ቀደም ሲል ከተተነበየው 3.1 በመቶ ዝቅ ብሎ ወደ 2.5 በመቶ ሊወርድ እንደሚችልና የነዳጅ ዋጋም በአማካይ እስከ 100 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

Popular Categories