ሙሉቀን የወንድወሰን ከዋሽንግተን ዲሲ
የIMF ልኡክ ግንቦት ላይ ኢትዮጵያን ይጎበኛል
የ4 አመቱን የኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈፃጸም አካል እና ለበጀት አመቱ ሁለተኛ የሆነውን ግምገማ ለማከናወን የIMF ልኡክ ከሳምንታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ይመጣል።
እንዲያም ሆኖ ግምገማውን ተከትሎ ማሻሻያው ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር በተደረሰው ስምምነት የክፍያ ሚዛን መደገፊያ ገንዘብ መለቀቅ ቢኖርበትም ያ እንደማይሆን ታውቋል።
5ኛ ዙር ግምገማውን ተከትሎ ወደ 260 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው ገንዘብ እንዲለቀቅለት የኢትዮጵያ መንግስት ለIMF ይፋዊ ጥያቄ አቅርቦ ያገኘሁት መረጃ ያረጋግጣል።
ሆኖም የገምጋሚ ቡድኑን የሚመሩት አልቫሮ ፕሪስ ባሳለፍነው ሳምንት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ቢሮዋቸው በነበረን ቃለ መጠይቅ ለ2018 በጀት አመት ከIMF የሚለቀቅ ገንዘብ እንደማይኖር አረጋግጠውልኛል።
የኢኮኖሚ ማሻሻያው በ2017 በጀት አመት ተግባራዊ መደረግ ሲጀምር IMF 3.4 ቢሊየን ዶላር ለክፍያ ሚዛን ማጠናከሪያ የሚሆን ብድር እንዲለቀቅ ማፅደቁ ይታወሳል።
ገንዘቡ የማሻሻያው አፈፃፀም እየታየ የሚሰጥ ሲሆን።
መሻሻያ ተግባራዉ መደረግ ሲጀምር ከተለቀቀው አንድ ቢሊየን ዶላር በመቀጠል በ4 ግምገማዎች የድጋፍ ገንዘብ በIMF ቦርድ እየፀደቀ ሲደገፍ ቆይቷል።
በዚህም የ4ኛ ዙር ግምገማን ተከትሎ ባለፈው ጥር ከተለቀቀው 261 ሚሊየን ዶላር ጋር በጠቅላላው ወደ 2.2 ቢሊየን ዶላር በማሻያው ሂደት የተለቀቀ ሲሆን።
በቀጣይ ወር የሚደረገውን የ5ኛ ዙር ግምገማ ተከትሎ ግን ለመጀት አመቱ የሚለቀቅ ገንዘብ አይኖርም ነው የተባለው።@seco


