ደጋፊዎች ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ጠይቀዋል
ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ በፒኤስጂ እና አርሰናል መካከል የሚደረገውን የዋንጫ ግጥሚያ ለመመልከት ነበር ልኡካቸውን ይዘው ወደ ቡዳፔስት ያቀኑት።
እንዲያም ሆኖ እንደሚመጡ አልተነገረንም እንዲሁም የኢቦላ ስጋት አለብን በሚል ሰበብ ከአውሮፕላን ጣቢያ እንዳይወጡ ተደርገዋል ነው የተባለው።
ጉዳዩ የዲፕሎማት መብቶችን ያለፈ መሆኑ ነው የተጠቀሰው።
በተመሳሳይ ከ52 አመታት በኋላ ለአለም ዋንጫ ያለፈውን የኮንጎ ብሄራዊ ቡድን ለመደገፍ ትኬት የገዙ ኮንጎአውያን ለትኬት የከፈልነው ገንዘብ ይመለስልን ሲሉ በእግር ኳስ ፌዴሬሽናቸው አማካኝነት ለፊፋ ጥያቄ ማቅረባቸው ተዘግቧል።

በኢቦላ ሰበብ የኮንጎ ደጋፊዎች ወደ አሜሪካ ለመምጣት እንዳያስቡ መባሉን ተከትሎ ነው ገንዘባችን ይመለስል የሚል ጥያቄ የቀረበው።
የቀድሞዋ ዛየር እኤአ በ1974 ለአለም ዋንጫ በመካፈል ከሰሀራ በታች የመጀመሪያዋ አገር ነች።
ከኳታሩ አለም ዋንጫ አንፃር ዘንድሮ የመግቢያ ትኬት እስከ 7 እጥፍ ጭማሪ የታየበት መሆኑ ታውቋል።
በነገራችን ላይ ፊፋ የኮንጎ ደጋፊዎችን ገንዘብ ለመመለስ እያጤነ መሆኑን አስታውቋል።@seco


