ዓለም አቀፍ አጋሮች ግንቦት 24 የተካሄደውን የኢትዮጵያ 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ መካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉ አስታወቁ

በኢቢቪ ዘጋቢ

 በምርጫው ሂደት ላይ የምርጫ ቦርድ፣ እጩዎች እና የሲቪል ማህበራት ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ እና የአባል አገራቱ ኤምባሲዎች፣ ከካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ጋር በመተባበር በጋራ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ምርጫ መካሄዱን  አድንቀዋል፡፡


ቡድኑ በመግለጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎች እና የሲቪል ማህበራት በምርጫው ሂደት  ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግኗል።


  የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ እንደ አለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ያላቸውን ሚና ጠቅሶ የመጨረሻ ሪፖርታቸውን በጉጉት እንደሚጠብቅ ገልጿል።


እንዲሁም ግንቦት 24 ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ ክልሎች በቀጣይ ዕድል እንደሚያገኙ ተስፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡


በሌላ በኩል የእንግሊዝ ኤምባሲ በኢትዮጵያ በምርጫ ማካሄድ  በተቻለባቸው አካባቢዎች የመርጫ ሂደቱ በሰላም መጠናቀቁን አመስግኗል።


ኤምባሲው እጩዎችን፣ የሲቪል ማህበራት ታዛቢዎችን፣ በጎ ፈቃደኞችን እና የምርጫ ቦርድን ጨምሮ ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉት  ጥረት አድናቆትን ችሯል። ኤምባሲው አፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ በምርጫው ያደረጉትን  የክትትል ሪፖርታቸውን እንደሚጠብቅ አስታውቋል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories