የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ባንኮችና ዲጂታል ገንዘቦች ላይ ያነጣጠረ 21ኛውን የማዕቀብ እቅድ ይፋ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ በሩሲያ ላይ የሚጥለውን 21ኛውን ከባድ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ረቂቅ ይፋ ማድረጉን የህብረቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት ካጃ ካላስ አስታወቁ።

ይህ አዲስ እቅድ በተለይ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ፣ የክሪፕቶ ፕላትፎርሞችን እና የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ማምረቻዎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚያናጋ ነው።

በዚህ ረቂቅ መሰረት 170 ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ማዕቀብ የሚጣል ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 90 የሚጠጉት የሩሲያ ባንኮች ናቸው። ይህም ህብረቱ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ባንኮች ላይ ማዕቀብ የጣለበት የመጀመሪያው አጋጣሚ ሲሆን፣ በማዕቀብ የተመቱትን የሩሲያ ባንኮች አጠቃላይ ቁጥር ከ100 በላይ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንኙነት ካላቸው የሀገሪቱ አበዳሪ ተቋማት መካከል ግማሽ ያህሉን ያጠቃልላል።

ማዕቀቡ የሀብት እገዳ፣ የጉዞ እና የገንዘብ ዝውውር እገዳዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ ውሳኔው እንዲጸድቅ የሁሉም የህብረቱ አባል ሀገራት ስምምነት ያስፈልገዋል።

የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች እንደገለጹት፣ የማዕቀቡ ዋና ዓላማ የሩሲያን የፋይናንስ ስርዓት በማዳከም ሞስኮ ከዩክሬን ጋር የሰላም ድርድር እንድታደርግ ግፊት ለመፍጠር ነው።

ባለፈው ዓመት የሩሲያ የኢኮኖሚ እድገት በከፍተኛ ወለድ እና በምዕራባውያን ማዕቀቦች ሳቢያ ወደ 1 በመቶ ዝቅ ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጥናት ተቋማትም የባንክ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል በስጋት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

ከባንኮች በተጨማሪ ማዕቀቡ ሩሲያ ገደቦችን ለማለፍ የምትጠቀምባቸውን 11 የክሪፕቶፕሌቶፎርሞችን የሚያካትት ሲሆን፣ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን እንደገለጹት፣ ይህ ውሳኔ ወደፊት በሶስተኛ ወገን ሀገራት ላይ ጭምር ሙሉ የክሪፕቶ አገልግሎት እገዳ ለመጣል መሰረት የሚጥል ነው።

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በርሜሉ ከ90 ዶላር በላይ እየተሸጠ ከሚገኘው የብሬንት ነዳጅ አንጻር፣ ህብረቱ የሩሲያ ድፍድፍ ነዳጅ የመሸጫ ዋጋ ጣሪያ አሁን ባለው 44 ዶላር ከ10 ሳንቲም ላይ ለስድስት ወራት እንዲቀዘቅዝ አቅዷል። ማዕቀቡ የሩሲያን የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦች፣ የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ሽያጭን፣ የዓሣ ምርት እና ለውትድርና አገልግሎት የሚውሉ የብረታ ብረት ውህዶችን የወጪና ገቢ ንግድ የሚገድቡ አዳዲስ ህጎችንም አካቷል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories