በኢቢቪ ዘጋቢ
ከከዚህ በፊቱ በተለየ ባንኮች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በCSD መላ አቅርበው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህም ከተሳተፉ 16 ባንኮች 8 ባንኮች በአማካኝ አንድን ዶላር በ158 ብር መግዛት ችለዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በ CSD ጨረታው ተሞክሮ በቴክኒክ ጉዳይ በሚል ጨረታው መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በጨረታው 100 ሚሊየን ዶላር የቀረበ ሲሆን የባንኮች ፍላጎት ግን 236.3 ሚሊየን ዶላር ነበር፡፡
ማእከላዊ ባንኩ ካለፈው በጀት አመት አንስቶ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ለማርካት በሚል በጨረታ ዶላር እንደሚሸጥ ይታወቃል፡፡
በCentral Security Depository/CSD የገንዘብ እና ድርሻ/ capital market ገበያውን ለማዘመን ወደ ስራ የገባ አዲስ መላ ሲሆን፡፡ አሁን ላይ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ እና የውጭ ምንዛሬ ግብይት እያደረጉበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ቀደም ባሉት የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች ባንኮች መወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በኢሜል እንደነበር ይታወሳል፡፡
አጋሮች ብሄራዊ ባንክ ጨረታዎን የሚያደርግበትን መንገድ በበለጠ ግልጽ እና ዘመናዊ እንዲያደርግ ሲመክሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ SECO

