ዘመን ባንክ “ዚ-ቀመር” የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ


የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ “ዚ-ቀመር” የተሰኘ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለማስጀመር ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡


ባንኩ ሁሉንም የማሕበረሰብ ክፍል የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት ከላቀ የደንበኞች አገልግሎት ጋር የተጣመረ በልህቀትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር እየተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህንን ተግባሩን ይበልጥ ለማሳደግ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ጠቁመው ይህም የፋይናንስ አካታችነትና የማሕበረሰብ ዕድገትን ለማረጋገጥ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ዘመን ባንክ የሸሪዓ መርሆዎችን መሠረት ያደረጉ የዚ-ቀመር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን ተለይተው በተዘጋጁ መስኮቶችና ሙሉ በሙሉ ለዚህ ተብለው በሚከፈቱ ቅርንጫፎቹ አማካይነት የሚሰጥ እንደሆነ የባንኩዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ አስታውቀዋል፡፡



የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር በበኩላቸው “ዚ-ቀመር” ከወለድ ነፃ አገልግሎት ለባንኩ አዳዲስ የገበያ እድሎችን የሚከፍት፤ የደንበኛ መሠረተረ የሚያሰፋ፥ የተቀማጭ ሀብት የሚያጠናክር እንደሆነ ተናግረዋል።
ባንኩ በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ባለው ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ጠንካራ ቦታ እንዲይዝ የሚያስችል ነው ገልፀዋል፡፡


የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን ዘመን ባንክ አዲስ በጀመረው የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓን መርሆዎችና ህግጋት በጥብቅ በማክበርና በመተግበር ለደንበኞች የላቀ አገልግሎት እንደሚሰጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የ”ዚ-ቀመር” ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አብራር ሽፋ ‘ዚ’ ዘመን ባንክን የሚወክል ሲሆን ቀመር ደግሞ ከአረብኛ ቃል የተወሰደና ትርጉሙም “ጨረቃ” ማለት እንደሆነና ውበትን፣ መረጋጋትንና ብርሃንን እንደሚያመለክት አስታውቀዋል።

ዚ ቀመር የህግ ማዕቀፎችንና የሸሪዓ ህግጋትን ሙሉ በሙሉ ያካተተ ሆኖ በመዘጋጀቱ ለደንበኞች ሁሉን አቀፍ፣ አስተማማኝና ትርጉም ያለው የፋይናንስ መፍትሄን እንደሚያቀርብ ጠቁመው ዘመን ባንክ እያደገ የመጣውን ከወለድ ነፃ የባንክአገልግሎት ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለደንበኞቹ ከእሴቶቻቸውና ከፋይናንስ ፍላጎታቸው ጋር የተጣጣመ የባንክ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ጨምረው ገልፀዋል።


የዚ-ቀመር መጀመር ባንኩ አካታች የፋይናንስ ሥነ-ምህዳርን ለመገንባትና የደንበኞችን ፍላጎቶች የሚያሟሉ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት ከፍ ያደርጋል ብለዋል።.SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories