የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የብሔራዊ የሎተሪ አስተዳደር የዕድል ጨዋታ ኦፕሬተር ከሆነው “ሁሉ ስፖርት” ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ሕጋዊ መሠረት የሌለው በማለት ውድቅ አደረገው። ይሁን እንጂ በተደረገ ይግባኝ እና የዕግድ ትእዛዝ ምክንያት ኩባንያው አሁንም ዝግ ሆኖ እንዲቆይ ተደርጓል።
ሁሉ ስፖርት መንግሥት 100 ቢሊዮን ብር ገቢ አጥቷል በሚል ካለፈው ታኅሣሥ ወር ጀምሮ ፈቃዳቸው ከታገደ 22 ኩባንያዎች አንዱ ነበር። ኩባንያው የፈቃድ ስረዛው የፍትሐዊ የሕግ ሂደት መብትን እና ንጹህ የመሆን መብትን የሚጻረር መሆኑን፣ እንዲሁም ያለ ምንም የፍርድ ቤት ውሳኔ እና የመሰማት ዕድል ቅጣት የተጣለበት መሆኑን በመጥቀስ ተከራክሯል።
በውሳኔው ላይ ግምገማ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ የገቢዎች ሚኒስቴርም እንደ ተከሳሽ ተካቷል።
ጉዳዩ አሁም በ15 ቀናት የዕግድ ትእዛዝ ጉዳዩ ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት መሄዱ ታውቋል። ፎርቹን እንደዘገበዉ ፤ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የቁጥጥር አካሉ ውሳኔ ሕጉን ያልተከተለ መሆኑን ቢገልጹም፣ የተደረገው ይግባኝ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለጊዜው አግዶታል።SECO


