የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ለ5 አመት ታገዱ

ተደጋጋሚ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ነበር ተብሏል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ፒኤችዲ) ከሳምንት በፊት ከሀላፊነታቸው ለተነሱት ተስፋዬ ቦሩ (ፒኤችዲ) በጻፉት ደብዳቤ በየትኛውም የባንክ ከፍተኛ ሃላፊነት በቀጣይ አምስት አመት ድርሽ እንዳይሉ መታገዳቸውን ገልጠዋል፡፡

ገዥው በፃፉት ደብዳቤ ባለፉት አምስት አመታት ሁለት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማእከላዊ ባንኩ ጽፎላቸው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ማእከላዊ ባንኩ ባለፈው ረቡዕ ሐምሌ 22 ባወጣው እና ኢቢቪ ባገኘው ደብዳቤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “እርስዎ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በሚመሩት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ላይ በተለይም በባንኩ ኮርፖሬት ገቨርናንስ፡ ብድር አሰጣጥና አስተዳደር የሰው ኃይል አመራር፣ የውጭ ምንዛሪ አፈቃቀድና አስተዳደር እንዲሁም የፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ልዩ ምርመራ ማድረጉን ተከትሎ የብሔራዊ ባንክን መመሪያዎች እና የባንኩን የውስጥ ፖሊሲና ፕሮሲጀር የጣሱ እና የባንኩን ጤናማ አሰራር የሚጎዱ በርካታ ጉድለቶች እና የህግ ጥሰቶች የተገኙ ሲሆን፣ በተከናወነው የምርመራ ግኝት ላይ ከባንኩ የቦርድ አመራር አባላት እና ከፍተኛ የሥራ አመራር አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ በአብዛኛው መግባባት ላይ መደረሱ እና በሪፖርቱ ግኝት ላይ ባንኩ ዝርዝር ምላሽ እና የድርጊት መርሐ ግብር ማቅረቡ ይታወሳል፣” ሲል ጠቅሶ፤

“በተከናወነው የምርመራ ግኝት እንዲሁም ከዚህ ቀደም ግንቦት 6 ቀን 2013 ዓ.ም እና ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከብሔራዊ ባንክ በተሰጠዎት ጥብቅ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ላይ በመመስረት በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 አንቀፅ 20 (1 እና 2) እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/89/2024 አንቀፅ 10 መሰረት ከዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢማ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የተሰናበቱ እና ከዚህ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አምስት አመታት በማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የፋይናንስ ተቋም ላይ የቦርድ አባል፤ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይም ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ ሆነው እንዳይሰሩ የታገዱ መሆኑን እናስታውቃለን፣” ሲል አክሏል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የባንኩ ቦርድ ተስፋዬን ከስራ ማሰናበቱ ይታወሳል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories