የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ወደ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ተሸጋገረ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) በይፋ”ፋይዳቨርስ” በመባል ወደ የመንግሥት የልማት ድርጅት ማዕቀፍ ማደጉ ተገለጸ።



ይህ አዲስ ድርጅት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ሥር የተጠቃለለ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ከነበረበት ማዕቀፍ ወጥቶ በንግድ አሠራር የሚመራ እና ዘላቂ ዲጂታል መሠረተ ልማት አቅራቢ ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የተቋቋመ መሆኑ ተጠቁሟል።



የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ እንደገለጹት፤ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ለቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ወሳኝ ድርሻ አለው።



ፕሮግራሙ አሁን ላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን መመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ 150 የሚደርሱ የንግድ ተቋማት የደንበኛ ማረጋገጫ (eKYC) ውህዶችን አከናውኗል። በተጨማሪም ከ190 ሚሊዮን በላይ ደህንነታቸው የተጠበቁ የማረጋገጫ ሂደቶችን በማከናወን ከ15 ሚሊዮን በላይ ዲጂታል መታወቂያ ምስክር ወረቀቶችን መስጠቱ ተገልጿል።



ተቋሙ አሁን የያዘውን አዲስ መዋቅር በመጠቀም የዲጂታል መታወቂያ መፍትሔዎችን ከአህጉራዊ አጀንዳዎች ማለትም ከአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና እና ከስማርት አፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እና አገልግሎቱን በክልሉ ለማስፋፋት ተነግሯል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories