የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በስፔስኤክስ አክሲዮን ዕድገት ምክንያት ዳግም ከ800 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለፈ

የስፔስኤክስ አክሲዮን በ15.8 በመቶ ማሻቀቡን ተከትሎ የኩባንያው የገበያ ዋጋ 1.75 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህንን ተከትሎም የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ 817 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም በፎርብስ መጽሔት 823.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።


የቅርብ ጊዜው የገበያ ንቅናቄ የመጣው ኩባንያው ካስመዘገበው ጠንካራ የሩብ ዓመት የገቢ አፈጻጸም በኋላ ሲሆን፣ የኩባንያው ገቢ ከታሰበው በላይ በመጨመር 7.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የኦፕሬቲንግ ኪሳራውም ወደ 541 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማለት ችሏል።

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት (AI) መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የ18.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ቢያደርግም፣ የባለሀብቶች እምነት ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል። የስታርሊንክ ሳላይት ኢንተርኔት ገቢ በ66 በመቶ አድጎ 4.29 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የክላውድ እና ኤአይ ክፍል ገቢ ደግሞ የ247 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

ስፔስኤክስ እጅግ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በታህሳስ ወር ዓመታዊ ገቢውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና እስከ 2030 ድረስ ደግሞ 1 ትሪሊዮን ዶላር ገቢ ለማስመዝገብ ግብ ማስቀመጡ ተመላክቷል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories