ኢትዮ ቴሌኮም አመታዊ ገቢውን 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ እንደሚሰራ አስታወቀ


ኩባንያው “ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂ ሁለተኛ አመት ዕቅዱን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።


በአለምሰገድ እስጢፋኖስ


የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳስታወቁት ካምፓኒው የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ አገራዊ ትስስርን ለማጎልበት፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የዳታ ፍጆታ ለማስተናገድ የሚያስፈልገውን አቅም ለመገንባት የሚያስችል የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።

ኩባንው በ2019 በጀት አመት የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና የደንበኞችን ተሞክሮ ለማሳደግ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት፣ ለማበልጸግ እና ለማዘመን የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ኢኒሸቲቮችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል።


በዚህም የዋየርለስ ቴክኖሎጂን፣ የፊክስድና የትራንስፖርት ኔትወርኮችን፣ የክላውድ እና የዳታ ሴንተር መሠረተ ልማቶችን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን እና የኢንፎርሜሽን ደህንነትን የሚያካትቱ ኢኒሸቲቮች በመተግበር ዋና ዓላማ የቴክኖሎጂ አቅምን ማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠን እና ኩባንያው በፈጠራ የታገዙ የዲጂታል ሶሉሽኖች መሪ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ እና ማዘመኛ መርሃ-ግብር ተግበሰራዊ በማድረግ የጠቅላላ ኔትወርክ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም ወደ 135 ነጥብ 7 ሚሊዮን እንደሚደርስ እንዲሁም የ4ጂ አቅም ደግሞ ወደ 35 ነጥብ 31 ሚሊዮን የአገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

የ 5ጂ አቅምን በእጥፍ በማሳደግ ከነጥብ 41 ሚሊየን ወደ 2 ነጥብ 70 ሚሊዮን እንደሚደርስ ጨምረው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር ማፋጠን በሚል ግልጽ ዓላማ በመንደፍ በ2019 በጀት ዓመት የኩባንያው አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ 295 ቢሊዮን ብር ለማድረስ መታቀዱን ነው የተናገሩት።

ይህም ከቀድሞው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ36ነጥብ 7 ብልጫ አለው ብለዋል።
ኩባንያችን ዓለም አቀፍ ቢዝነሱን እና የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎቶችን እንዲሁም የመሠረተ ልማት መጋራትን በማስፋፋት የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ዲጂታል ትስስርና የውጭ ምንዛሪ የማመንጨት አቅም በማጠናከር 253 ነጥብ 7 ሚሊየን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories