በ2018 ዓመት በኤክስፖርት 390 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱንም በበዓመታዊ የቤተሰብ ቀን በዓሉ ላይ አስታውቋል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀን በወዳጅነት አደባባይ መስከረም 7/2019 ባከበረበት ወቅት የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ በ2018 በጀት ዓመት 390 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት ቢዝነስ ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 67 ነጥብ 11 ቢለየን ብር ለማግኘት አቅዶ የነበረው ሚድሮክ እቅዱን 98 በመቶ ማሳካቱንም አቶ ጀማል ተናግረዋል፡፡
በወርቅ ልማት ስሙ የሚታወቀው ሚድሮክ ከማዕድን ዘርፍ 6 ነጥብ 47 ቢሊየን ብር ያገኘ ሲሆን ከእቅዱ ግን የፈፀመው 67 በመቶውን ነው።

የአመራሩና የሰራተኛው ተናቦ መስራት ግሩፑን ውጤታማ አድርጎታል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሚድሮክ በ2018 ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 700 ሠራተኞች ቦነስ መስጠቱን እና በአጠቃላይ 1.2 ቢሊዮን ብር ቦነስ ማበርከቱን አስታውቀወል፡፡
በአመታዊ የሰራተኞች በዓል ላይ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ መንበር ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በቀጥታ የቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገሪቱ የላቀ እድገት እንድታስመዘግብ ሚድሮክ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
ሚድሮክ አሁን አዳዲስ ፕሮጀክቶችንም በቀጣይ በማከናወን ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሰራ ባለሃብቱ ገልጸዋል።SECO


