በአፍሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ መስፋፋትን ተክተሎ በየተቋማቱ ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች በከፍተኛ መጠን መጨመራቸውን ማስተርካርድ ያደረገዉ ጥናት ቅዳሜ ገበያ ተመልክቷል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ እ.ኤ.አ. በ2025 ብቻ አህጉሪቱ 69,236 የሳይበር ጥቃቶች አስተናግዳለች፤ ይህም በየስምንት ደቂቃው አንድ ጥቃት ይፈጸም እንደነበር አሳይቷል።
እ.ኤ.አ. ከ2016 እስከ 2025 ባሉት ዓመታት ውስጥ በአፍሪካ የሳይበር ጥቃት በ421 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ ይህም ከዓለም አቀፉ የ307 በመቶ እድገት በእጅጉ ይበልጣል ብሏል።
በዚሁ ጊዜ ውስጥ የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚዎች በ5.9 እጥፍ ያደጉ ሲሆን፣ የዲጂታል ክፍያ ኢኮኖሚው እ.ኤ.አ. በ2030 1.5 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከጥቃቶቹ መካከል 44 በመቶ ያህሉ በቴክኖሎጂ፣ በመንግስት እና በፋይናንስ ተቋማት ላይ የተሰነዘሩ መሆናቸውን ማስተማር ካርድ አመልክቷል።SECO


