ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል

የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቦታዎችን በማቋቋም የአመራር መዋቅሩን እንደገና ማደራጀቱን ETBusinessView ከታማኝ ምንጮች ሰምቷል።

መንግሥታዊ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት አዲሱ መዋቅር ሰኞ ምሽት ለኩባንያው አመራሮች ይፋ መደረጉን ምንጮች ለETBusinessView ገልጸዋል። መዋቅሩ የድርጅቱን ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች በቴክኖሎጂና ኦፕሬሽን፣ በንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በሀብት አስተዳደርና የኮርፖሬት አገልግሎቶች በሚል በሦስት ዋና ክፍሎች ይከፍላል።

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም የኢንፎርሜሽን ሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ፀጋዬ ኤማኑኤል የቴክኖሎጂና ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተመድበዋል። እርሳቸውም ወደ አምስት የሚጠጉ የቴክኒክ ክፍሎችን እንደሚመሩ ምንጮች ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም የድርጅቱ ዋና የግብይት ኃላፊ የነበሩት ሰኢድ አራጋው የንግድ ክፍሉን እንዲመሩ ተመድበዋል። ይህ ክፍል ግብይትን፣ ሽያጭንና ተያያዥ ሥራዎችን ያካትታል።

በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የፋሲሊቲና የተሽከርካሪዎች አስተዳደር ኃላፊ የነበሩት አይናለም አልበኔ የሀብት አስተዳደርና የድርጅት አገልግሎቶች ክፍልን እንዲመሩ ተመድበዋል።

ምንጮች እንደገለጹት ሦስቱም ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች በተጠባባቂነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ ይህ ሹመት የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ ፍሬሕይወት ታምሩ ዓርብ ታሪኩ ደምሴን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው ከመመደባቸው በኋላ የተከናወነ ነው።

ፋይናንስ፣ የድርጅት ጉዳዮችና ኮሙኒኬሽን፣ የደንበኞች ተሞክሮና እና ትራንስፎርሜንሽን፣ እንዲሁም ስትራቴጂና የቁጥጥር ጉዳዮች (strategy and regulatory affairs) በቀጥታ በዋና ሥራ አስፈጻሚው ሥር እንደሚቆዩ ምንጮቹ ገልጸዋል።

አዲሱ መዋቅር ከሦስቱ የምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቦታዎች መፈጠር በተጨማሪ የኃላፊነት ክፍፍልንና የአንዳንድ የአመራር የሥራ መደቦችን ስያሜ መቀየር እንደሚያካትት ምንጮቹ አስረድተዋል።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ የምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቦታዎች እ.ኤ.አ. በ2010 የፈረንሳዩ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ኦራንጅ በድርጅቱ የበላይ ሆኖ ከመጣ በኋላ ከመዋቅሩ ተወግደው ነበር።

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከመቀየሩ በፊት በአማረ አምሳሉ የአመራር ዘመን ፍሬሕይወት ታምሩ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዳገለገሉ ምንጮች አስታውሰዋል፡፡

ፍሬሕይወት ከዚያ በኋላ ድርጅቱን ለቀው የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ንግድ እንደመሠረቱ ተገልጿል። በኋላም ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተመልሰው ድርጅቱን ለ 8 አመታት በውጤታማነት መርተው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሆኖም ቴሌኮም ኩባንያውን የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲመሩ መቀመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

ታከለ ኡማ እና የኢትዮ ቴሌኮም

በሌላ በኩል፣ ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኑት ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል የሚል ወሬ ተሰራጭቷል።

ሆኖም ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ለETBusinessView እንደገለጹት፣ ወሬው ሙሉ በሙሉ የተፈጠራ ነው ሲሉ ነው ያጣጣሉት፡፡

በኢትዮ ቴሌኮም አመራር ውስጥ ያሉ ምንጮችም ታከለ ኡማ ተሹመዋል የሚለው መረጃ ሐሰት መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአመራር መዋቅሩ ለውጥ በተካሄደበት ወቅት የተሰራጨው ይህ ወሬ፣ በድርጅቱ የከፍተኛ አመራር ላይ ጥያቄዎችን ቢያስነሳም፣ የሦስቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ምደባ እና የኃላፊነት ክፍፍሉ የድርጅቱ ዋና የአደረጃጀት ለውጥ ሆኖ ቀርቧል ነው የተባለው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories