በአዲስ አበባ ከተማ ለኤሌክትሪክ ባስ አገልግሎት የሚውል ፈጣን መንገድ ሊገነባእንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ነው የገለጸው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን እንደገለጹት ፈጣን መንገዱ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን እና በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በጋራ የሚገነባ ነው ።
መንጠዱ15 ነጥብ 64 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።
ፕሮጀክቱ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶች የያዘ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በቀን 400 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ገልጸው፤ በየመዳሻዎቹ ከአንድ እስከ 15 ደቂቃ ባለው ጊዜ የሚደርስ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ርዝመት ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም ያሉትን መንገዶች የሚሸፍን ሲሆን ወጪውም የከተማው አስተዳደር እንዲሁም በአጋርድርጅቶች እንደሚሸፈን የዘገበው ኢፕድ ነው።


