ማእከላዊ ባንክ ዶላር በወቅቱ የማያስገቡ ላይ እርምጃ እወስዳለው አለ

ጉዳዩ ከክፍያ ስርአት ጋር የሚገናኝ ነው በቶሎ ይታረም ሲሉ ባለሞያዎች አሳስበዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ (ኢብባ) ሸቀጥ ልከው የውጭ ምንዛሬውን በወቅቱ የማያስገቡ ነጋዴዎችን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ፡፡ ችግሩ የተፈጠረው መንግስት የካሽ አጌነስት ዶክመት/ cash against document (CAD) አሰራር ተግባራዊ በመደረጉ ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሞያዎች ተናገረዋል፡፡

ዛሬ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓም የብሄራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ፒኤችዲ) በተገኙበት ከማህበራት ሃላፊዎች እና ከተመረጡ ላኪዎች ጋር ስብሰባ ማድረጉን የገለፀው ማእከላዊ ባንኩ በወጪ ንግድ የተገኘን ገንዘብ በወቅቱ ወደ አገር ከማገባት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች እንዲፈቱ አሳስቧል፡፡

ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ በፊት ውይይት ያስፈልጋል በሚል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን የጠቀሰው ኢብባ ላኪዎች ያገኙትን የውጭ ምንዛሬ በቶሎ ያስገቡ ሲል ነው ጥሪ ያስተላለፈው፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሞያዎች እና ላኪዎች በበኩላቸው መንግስት የCAD አሰራር መተግበሩ የፈጠረው ችግር ነው ሲሉ ነው የገለፁት፡፡

በቀደመው አሰራር የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ አስተማማኝ በሆነው የባንክ መተማመኛ ሰነድ/letter of credit (LC) ብቻ ይሰተናድ እንደነበር አስታውሰው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰነድ ባንክ ከደረሰ በኋላ በሚያስከፍለው አሰራር ማለትም CAD ሸቀጥ ወደ ውጭ እንዲላክ በመፈቀዱ በርካታ ግለሰቦች እና ነጋዴዎች ገንዘብ ለማሸሽ እንደተጠቀሙበት ነው የጠቀሱት፡፡

ጉዳዩ በማይመለከታቸው እና በተለያዩ ግለሰቦች ስም ንግድ ፈቃድ አውጥተው እቃ በመላክ የተገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር ከማስገባት ይልቅ እዛው እንዲቀር በማድረግ በርካቶች ተሳትፈዋል የሚሉት የዘርፉ ባለሞያዎች፡፡

በህገወጥ ተግባዉ የተሳጠፉ ድርጅታቸውን ዘግተው ጠፍተዋል ሲሉ ነው የጠቀሱት

ቀደም ሲል አገሪቱ ለCAD የክፍያ አሰራር አልተዘጋጀችም ሲባል እንደነበር ጠቅሰው መንግስት ለምን ይሄን አሰራር ፈቀደ ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

በኢብባ ስብሰባ ከቡና፣ ሰሊጥ እና ጥራጥሬ ላኪዎች ጋር ውይይት መደረጉ የተገለፀ ሲሆን፡፡

ዘርፉን የሚከታተሉ ባለሞያዎች እና ላኪዎች ችግሩ በዋናነት ከቡና ላኪዎች ጋር በተያያዘ በስፋት መከሰቱን ጠቅሰዋል፡፡

አሁንም ቢሆን መንግስት በ CAD የሚላክ እቃ ላይ የገንዘብ መጠን ወይም የሸቀጥ መጠን ላይ ጣራ ማበጀት አለበት ሲሉ ነው ያሳሰቡት፡፡   

cash against document (CAD)

letter of credit (LC)

ሰነዱ ባንክ ከደረሰ በኋላ ክፍያውን ይከፍልሃል

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories