ጥገና ላይ የሰነበተው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ስኳር የማምረት ሥራውን ይጀምራል ተባለ

የክረምት ወቅት ጥገና ሲደረግለት የሰነበተው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ከሕዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ስኳር የማምረት ሥራውን ይጀምራል።

ሸንኮራ አገዳ ወደ ፋብሪካው የሚያጓጉዙ ማሽነሪዎች እና የፋብሪካው የጥገና ሥራ መጠናቀቁን የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እዩኤል ለላንጎ ተናግረዋል።

በዲዛይን ካፓሲቲው መሠረት የፋብሪካው በቀን ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት ዐቅም 6 ሺህ 250 ቶን መሆኑን ገልጸው፥ ያለውን የሸንኮራ አገዳ አቅርቦትና ሌሎች ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ በቀን 4 ሺህ 890 ቶን ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት ሥራውን ይቀጥላል ብለዋል።

በዓመት 601 ሺህ 574 ነጥብ 25 ቶን ሸንኮራ አገዳ በመፍጨት 70 ሺህ 239 ነጥብ 8 ቶን ስኳር እንደሚያመርትም አስገንዝበዋል።

ፋብሪካው በሙሉ ዐቅሙ ሸንኮራ አገዳ መፍጨት እንዲችል በአርሶ አደር ማሳ ተጨማሪ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ለማልማት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የሸንኮራ አገዳዎችን ዝርያ የማሻሻል፣ሸንኮራ አገዳ የመፍጨት፣ ስኳር የማምረት ዐቅምና የጨመቃ ሂደት ላይ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች በጥገና ወቅት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

ለዘንድሮው ስኳር የማምረት ሥራ በአማካይ 13 ነጥብ 9 በመቶ የስኳር ይዘት ያለው የሸንኮራ አገዳ ዝርያ ለፋብሪካው እንደሚቀርብም ተናግረዋል ሲሉ የዘገበው ኢዜአ ነው።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories