በስርቆትና ውድመት የተነሳ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከ114 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት እና የኃይል ስርቆት ላይ የደረሰበትን ጉዳት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

 ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር፤ ባለፉት አራት ወራት በመሰረተ ልማት በተፈጸመ ስርቆት፣ በመኪና አደጋ በደረሰ ውድመት እና በኃይል ስርቆት በድምሩ 114 ሚሊዮን 299 ሺህ 93 ብር የሚገመት ጉዳት በተቋሙ ላይ ደርሷል ብለዋል።

በ17 ትራንስፎርመሮች ላይ በተፈጸመ ስርቆት 23 ሚሊዮን 85 ሺህ 847 ብር ኪሳራ ደርሷል ያሉት ኃላፊው፤ በኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ ኬብል ስርቆት ደግሞ 88 ሚሊዮን 849 ሺህ 858 ብር ጉዳት ደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።

በመኪና ግጭት የደረሰ የመሠረተ ልማት ውድመት ብዛት 15 ሲሆን፣ በብር ሲተመን 18 ሚሊዮን 178 ሺህ 731 ብር ጉዳት ማጋጠሙን አብራርተዋል።

ተቋሙ ባለፉት አራት ወራት 36 ነጥብ 45 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት መፈጸሙን ጠቁመው፤ በዚህም ምክንያት ተቋሙ 13 ሚሊዮን 184 ሺህ 677 ብር አጥቷል ሲሉ አብራርተዋል።

በአጠቃላይ ባለፉት አራት ወራት 107 ጉዳቶች እንደተመዘገቡ ጠቅሰው፤ 10 የወንጀል ክሶች ተመስርተው በፍርድ ሂደት ላይ እንደሚገኙ፣ ቀሪዎቹም በፖሊስ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የዘገበው ኢፕድ ነው።Seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories