በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በነበረው የብሪክስ አገራት “ዊል ፎር ፒስ 2026” (Will For Peace 2026) የባሕር ላይ ልምምድ ላይ ሲሳተፍ የነበረው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልዑካን ቡድን ወደ አገሩ ተመልሷል።
የልዑካን ቡድኑ መሪ ምክትል አድሚራል ክንዱ ገዙ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በልምምዱ ወቅት ከብሪክስ አባል አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ ጠቃሚ ግብዓቶችን አግኝታለች።
ከዚሁ ልምምድ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ ከደቡብ አፍሪካ ባሕር ኃይል አቻቸውና ከሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል በተለያዩ የሥልጠና ዘርፎች ለመደገፍና አቅሙን ለማጠናከር የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ መደረሱን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል ግንባታ ይበልጥ ለማቀላጠፍ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።@SECO


