የማዳበሪያ መሸጫ ዋጋ አለመወሰን በበልግ እርሻ ላይ ስጋት ደቀነ

የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው የማዳበሪያ መሸጫ ዋጋን ለመወሰን በመዘግየቱ ምክንያት፣ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በወቅቱ ለመዝራት መቸገራቸውና ይህም በበልግ ወቅት በሚገኘው ምርት ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት ተፈጠረ።

 የማዕከላዊ ባንክ ገዥን እና የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን በአባልነት የያዘው የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ፣ ከየካቲት እስከ ሚያዝያ ለሚዘልቀው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች አርሶ አደሩ ማዳበሪያውን የሚገዛበትን የዋጋ ተመን እስካሁን አላሳወቀም።

​የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሰባት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለፓርላማው የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ባለፈው ዓመት ተገዝቶ ያልተሰራጨ 4 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መጋዘኖች ውስጥ ይገኛል።

ይሁን እንጂ የዋጋ ተመኑ ባለመወሰኑ ማዳበሪያው ወደ አርሶ አደሩ ሊሰራጭ አልቻለም። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ እንደተናገሩት፣ ማዳበሪያው በመጋዘን ተከማችቶ እያለ በዋጋ ውሳኔ መዘግየት ምክንያት ለአርሶ አደሩ አለመድረሱ በበልግ ወቅት የሚመረቱ እንደ ስንዴ እና ገብስ ያሉ አጫጭር የሰብል ዓይነቶች ላይ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤ ​ይህ በዋጋ ውሳኔ ላይ የታየው መዘግየት በአርሶ አደሩ ዘንድ ትልቅ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን፣ መንግስት ለአቅርቦቱ ትኩረት ሰጥቶ ፈጣን ውሳኔ ካላሳለፈ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ጥረት ሊያደናቅፍ እንደሚችል ተጠቁሟል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories