የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኦልድ ታህ እንደገለጹት ባንኩ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የአፍሪካ አገራት ድጋፍ የሚውል 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡን ይፋ አድርገዋል።
ይህ በታሪክ ከፍተኛ የተባለው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት፣ አፍሪካ በውጭ ዕርዳታ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስና “New African Financial Architecture (NAFA)” በተሰኘው አዲስ ስትራቴጂ አማካኝነት የራሷን የውስጥ ሃብት በመጠቀም የፋይናንስ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለጀመረችው ጉዞ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ትኩረታቸው የወጣቱን የሰው ሃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ፀጋ መቀየር፣ የተፈጥሮ ሃብትን እሴት መጨመር እና በአህጉሪቱ ያለውን የፋይናንስ ክፍተት መሙላት ላይ እንደሚሆን ገልጸዋል።@SECO


