የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር የአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦት ወደ ነበረበት ለመመለስ ወራትን ሊፈጅ ይችላል አለ

በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በኩል የነዳጅ ትራንስፖርት ቢጀመር እንኳ፣ የአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦትና ዋጋ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ ወራትን እንደሚወስድ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) አስታወቀ።

የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ዊሊ ዎልሽ እንደገለጹት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ምክንያት በነዳጅ ማጣሪያ አቅም ላይ የደረሰው መስተጓጎል አቅርቦቱን በፍጥነት ለማስተካከል እንቅፋት ሆኗል። “ሁኔታው በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይስተካከላል ብዬ አላስብም፤ ወራትን ሊፈጅ ይችላል” ብለዋል።

አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ ረቡዕ ዕለት የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ ስምምነት የተደረሰው የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሰጡት የጊዜ ገደብ ሊያበቃ አንድ ሰዓት ሲቀረው ነው።

 ስምምነቱ ቴህራን ለዓለም አቀፍ ነዳጅና ጋዝ ዝውውር ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ለጊዜው እንድትከፍት ያስችላታል።

ምንም እንኳ ድፍድፍ ነዳጅ በድጋሚ መፍሰስ ቢጀምርም፣ የማጣራት አቅሙ በመስተጓጎሉ ችግሩ ለተወሰነ ጊዜ እንደሚቀጥል ዎልሽ አስረድተዋል።

“ኢንዱስትሪው ለነዳጅ ዋጋ መጨመር የሚሰጠው ምላሽ የታሪፍ ዋጋን በመጨመር ነው፤ ይህ ደግሞ የማይቀር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ቀውስ ምክንያት የተቀየሩ የበረራ መስመሮችን በተመለከተ ሲያስረዱ፣ ሌሎች አየር መንገዶች የባህረ ሰላጤው አየር መንገዶችን የመሸከም አቅም ሙሉ በሙሉ ሊተኩ እንደማይችሉና ማዕከላቱ በፍጥነት ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories