የናፍጣ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል! – የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ

በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አሳውቀዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ምክንያት በተፈጠረው የዋጋ መጨመር እና የአቅርቦት መስተጓጎል የተነሳ በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ ነበር።

አሁን የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ ቀደመው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ እንደሚጀመር የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ወደ ክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ መጓጓዝ ይጀምራል ብለዋል።

እስካሁን የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ በነበረው መጠን እየቀረበ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመከላከል መንግሥት በልዩ ግዢ በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ ገዝቶ እያቀረበ መሆኑንም ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አስረድተዋል።

በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት መንግሥት በየወሩ ቀድሞ ከነበረው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር እየደጎመ ነዳጅ እያቀረበ መሆኑን ነው የገለፁት።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories