ዳሽን ቢራ ፋብሪካ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾመ

የዳሽን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ቦርድ አቶ ማትያስ ጌታቸውን አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል።

ሹመቱ ካለፈዉ ከሰኞ ሚያዝያ 19 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ሹመቱ ደግሞ በታሪክ በውጭ አገር ዜጎች በሚመራው የቢራ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ አንድን ትልቅ ኩባንያ ለመምራት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሥራ አስፈጻሚ በመሆናቸው ለዘርፉ ትልቅ ታሪካዊ ሽግግር ተደርጎ ተወስዷል።

አቶ ማትያስ እ.ኤ.አ. በ2020 በዋና የፋይናንስ ኦፊሰርነት (CFO) ዳሽንን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በቆይታቸውም የኩባንያውን የፋይናንስ አቋም በማጠናከር፣ ስልታዊ ውሳኔዎችን በመደገፍ እና ጠንካራ የአሠራር ሥርዓት በማስፈን ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።

ከጥቅምት 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ማትያስ፣ በዚህ የሽግግር ወቅት ፈታኝ የሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ቢኖሩም የምርት ብቃትን በማሳደግ፣ የሽያጭ ዕድገትን በማስመዝገብ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠር ረገድ ውጤታማ መሪነታቸውን አስመስክረዋል።

አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደ SABMiller፣ Coca-Cola Beverages Africa እና Diageo ባሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ የመሪነት ሚናዎችን የተጫወቱ በመሆናቸው ሰፊ ልምድ ይዘው ወደ ኃላፊነቱ መምጣቱን ለቅዳሜ ገበያ ከተቋሙ የደረሰው መግለጫ ያመለክታል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ከሄሪዮት ዋት (Heriot-Watt) ዩኒቨርሲቲ በማስተርስ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፣ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያ (ACCA) ናቸው።

ከ25 ዓመታት በፊት በጎንደር ከተማ በጥረት/ኒጋት ኮርፖሬት የተመሰረተው ዳሽን ቢራ፣ እ.ኤ.አ. በ2011 ከለንደኑ ዱኤት ቫሳሪ (Duet Vasari) ጋር በጋራ በመሆን በደብረ ብርሃን ሌላ ፋብሪካ በመገንባት አቅሙን አስፋፍቷል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories