በኢቢቪ ዘጋቢ
የባህረ ሰላጤው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው ልዮ ጨረታ 30 ባንኮች ሲሳተፉ 14 ባንኮች ጨረታውን ማሸነፍ ችለዋል፡፡
ዛሬ በተካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አማካኝ ዋጋ 159.98 በዶላር ሲሆን ይህም ከሁለት ወር በኋላ የብር የመግዛትን አቅም በ1.6 በመቶ አዳክሞታል፡፡
ባለፉት ሁለት ወራት የባህረ ሰላጤው ጦርነት መነሳት ምክንያት የውጭ ምንዛሬ ሳካሄድ ቆይቷል፡፡ በጠቅላላው 140 ሚሊየን ዶላር በመደበኛ ጨረታ የተሸጠ ሲሆን ዛሬ የተካሄደውን 4ተኛ ልዩ ጨረታ ጨምሮ 1.65 ቢሊዮን ዶላር ለባንኮች ተሸጧል፡፡
በበጀት አመቱ በአጠቃላይ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ለባንኮች በጨረታ ቀርቦ ነበር፡፡@seco


