የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ለዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የሚውል የ1.776 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሙን አስታወቀ

የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ባለፈው የጆ ባይደን አስተዳደር ዘመን “በፖለቲካ ምክንያት ያለአግባብ ጥቃት ደርሶብናል” ለሚሉ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አጋሮችና ደጋፊዎች ካሳ የሚከፍል የ1.776 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሙን አስታውቋል።

ይህ ከታክስ ከፋዮች ገንዘብ የሚሸፈነው እና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ፤ ትራምፕ በገዛ እጃቸው በሚቆጣጠሩት የመንግስት ተቋም በኩል ለደጋፊዎቻቸው ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል በመሆኑ በዴሞክራቶች እና በሙስና መከላከል ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ትችትና ህጋዊ ክስ ሊገጥመው እንደሚችል ተገልጿል።

“የፀረ-መንግስት መሳሪያነት” የተሰኘውና የአሜሪካን የነፃነት አዋጅ ዓመተ-ምህረትን (1776) በምሳሌነት የያዘው ይህ ፈንድ ይፋ የሆነው ዶናልድ ትራምፕ በግል ማንነታቸው በገቢዎች ባለስልጣን ላይ የመሰረቱትን የ10 ቢሊዮን ዶላር ክስ በፈቃደኝነት ማቋረጣቸውን ተከትሎ ነው።

በስምምነቱ መሰረት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ምንም አይነት ቀጥተኛ የገንዘብ ክፍያ የማይደረግላቸው ቢሆንም፣ ፍትህ ሚኒስቴር ግን ይፋዊ ይቅርታ ይጠይቃቸዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር ጊዜያዊ ዋና አቃቤ ህግ እና የቀድሞው የትራምፕ የግል ጠበቃ ቶድ ብላንች በሰጡት መግለጫ፣ የመንግስት መዋቅር በማንኛውም አሜሪካዊ ላይ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ መሆን እንደሌለበትና ፈንዱ ቀደም ሲል የተፈጸሙ ስህተቶችን ለማረም ህጋዊ አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል።

ፈንዱን የሚያስተዳድረውን ባለ አምስት አባላት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ትራምፕ የመሻርና የማባረር ሙሉ ስልጣን የሚኖራቸው ሲሆን፣ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረቢያው ጊዜ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2028 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ይሁን እንጂ ትራምፕ ክሱን ከማቋረጣቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት100 የሚሆኑ የኮንግረስ ዴሞክራቶች ለፍርድ ቤት ባስገቡት ሰነድ ፕሬዝዳንቱ የግል ጥቅምን ማስከበር ላይ ያተኮረ ግልጽ አድሎአዊ አሰራር እየፈጸሙ ነው ሲሉ ከሰዋል።

ይህ ስምምነት እንደ ማይክል ፍሊን እና ካርተር ፔጅ ያሉ የትራምፕ የቅርብ አጋሮች ከዚህ ቀደም ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር ካደረጓቸው የሚሊዮን ዶላር የካሳ ስምምነቶች ቀጥሎ የተመዘገበ ትልቅ ክስተት ሆኗል።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories