በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ያካበቱ የስራ ኃላፊዎችን በጠንካራ የውድድር ሂደት በመመልመልና ምርጫ በማካሄድ አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አማራ ባንክ አስታወቀ

ባንኩ ለቅዳሜ ገበያ በላከው መግለጫ አማራ ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቋም ሆኖ ቀጥሏል።

የባንኩ እድገት የአንድ ግለሰብ፣ የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ውሳኔ ውጤት ብቻ ሳይሆን በጋራ ኃላፊነት እና በጠንካራ ተቋማዊ መሠረት የተገነባ በፋይናንስ ዘርፍ በአገር-አቀፍ ብሎም በአለምአቀፍ ብቁ ተወዳዳሪ እና ብራንድ የመሆን ራዕይን ሰንቆ የተመሰረተ ባንክ እንደሆነ አስታውቋል።

አማራ ባንክ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት፡ የባለአክሲዮኖቹን እምነት፣ የደንበኞቹን ጥቅም እና የተቋሙን ተአማኒነት በማስጠበቅ የባንኩን ሥራ በሕግ፣ በሥርዓት እና በተቋማዊ መርሆዎች መሠረት ለማከናወን ቁርጠኛ መሆኑን ለሁሉም ባለደርሻ አካላት ማረጋገጥ እንወዳለን ብሏል።

የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ራዕይ፡ ተልዕኮ እና ስትራቴጂ በውጤታማነት ሊመሩ የሚችሉ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ያካበቱ የስራ ኃላፊዎችን መመሪያን እና ግልጽ መርህን በተከተለ እና በጠንካራ የውድድር ሂደት በመመልመልና ምርጫ በማካሄድ አደራጅቶ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ባንኩ ስራውን በተገቢው መንገድ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቆ ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያ መሰረተ-ቢስ እና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በባንኩ አመራር አባላት እና በባንኩ ደንበኞችም ጭምር የሀሰት መረጃ በማሰራጨት መልካም ስምን የሚያጎድፍ እና የባንኩን ገጽታ የሚያጠለሽ ተግባር እየተፈፀመ ነው ሲል ከሷልል።

የባንኩ ከፍተኛ አመራር ምልመላና ምርጫ ሂደት በቦርዱ በፀደቁ የኮርፖሬት ገቨርናንስ መመሪያዎች፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተፈጻሚ በሆኑ መመሪያዎችና መስፈርቶች መሠረት ብሎም በተቋሙ የውስጥ አሠራር ስርዓቶች መሠረት ደረጃ በደረጃ መከናወኑን አስታውቋል።

ሂደቱም በብቃት፣ በሙያዊ ብስለት፣ በተገቢ ምዘና እና የአመራር ብቃትን መሰረት ባደረጉ መስፈርቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ በየደረጃው የተሰጡ ውሳኔዎችም በህጋዊና ተቋማዊ ሂደት መመራቱን ባንኩ በመግለጫው ገልጿል።

የቦርዱ ምልመላ፣መረጣና ክፍያ ኮሚቴ በመደበኛ አሰራር ተዋቅሮ ሥራውን አከናውኗል ።ለሁሉም የቦርድ አባላት እጩዎችን በተቀመጠው ጊዜ የመጠቆም እኩል ዕድል ተሰጥቷል፣የምልመላ እና መረጣ ሂደቱን ዝርዝር ሂደት የሚግልጽ መመሪያ ተዘጋጅቶ ቦርዱ አጽድቋል።

የተጠቆሙ እጩዎች የትምህርት፣ የሙያ እና የአመራር ብቃት በጸደቀው መመሪያ እና በተዘጋጁ መስፈርቶች መሠረት መገምገማቸውና ለእጩ ተወዳዳሪዎችን የቅድመ ልየታ (በብሄራዊ ባንክ ዝቅተኛ መስፈርት መሰረት)፣ እንደእየ እጩ ተወዳዳሪዎች መደብ የመወዳደሪያ ስትራቴጅ ዝግጀት፡ የገለጻ፣ የቃለ መጠይቅ እና ለሁሉም እጩ ተውዳዳሪዎች ጥልቅ የሆነ የኋላ ታሪክ ምርመራ በሚገባ እና በተደራጀ አግባብ ተከናውኗል።

የምልመላ እና መረጣ ሂደቱን በግልጽ የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት ከበርካታ ደጋፊ ሰነዶች ጋር ለዳይሬክተሮች ቦርድ ለውሳኔ መቅረቡን ጠቁሞ የመጨረሻ ውሳኔም በዳይሬክተሮች ቦርድ ሕጋዊ ሥልጣን መሠረት በውይይት እና በድምጽ ብልጫ ውሳኔ በመስጠት ባንኩን በቀጣይ የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮችን እንደመረጠ ባንኩ አስታውቋል።

አማራ ባንክ ጤናማ የሀሳብ ልዩነት፣ ሙያዊ ክርክር እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ውይይትን የሚያከብር ቢሆንም፣ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ያልተረጋገጡ መረጃዎች፣ የተሳሳቱ ትርጓሜዎች ወይም የተቋሙን ስም እና የባንኩ የበላይ ሃላፊዎችን ክብር የሚጎዱ መረጃዎች በሕዝብ ዘንድ መሰራጨታቸው ለተቋሙ እና ለፋይናንስ ዘርፉ አጠቃላይ መረጋጋት የማይጠቅም መሆኑን በፅኑ ያምናል። ይህንን ኃላፊነት የጎደለው ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ሲል አስጠንቅቋል።

ባንኩ በቀጣይም ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣ መልካም አስተዳደርን እና ተቋማዊ ጥንካሬን በማስፈን የተጀመረውን የእድገት ጉዞ ለማስቀጠል በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ ያረጋግጣል።

ባንኩ ትኩረቱን በወጀብ እና በውዝግቦች ላይ ሳይሆን በእድገት፣ በአዳዲስ አገልግሎቶች፣ በዲጂታል ለውጥ፣ በደንበኞች እርካታ እና በአገራዊ ኢኮኖሚ ላይ በሚያበረክተው አስተዋፅኦ ላይ ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራና በቀጣይም የእድገት ጉዞውን በጥንካሬ እንደሚቀጥል ባንኩ ሙሉ እምነት እንዳለው አስታውቋል።

የአማራ ባንክ ጥንካሬ የሁላችንም የጋራ ጥንካሬ ነው። የባንኩ ስኬት የባለአክሲዮኖች፣ የደንበኞች፣ የሰራተኞች እና የአገራችን ስኬት ነው። ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተረጋገጠ መረጃ ላይ በመመርኮዝ ለተቋሙ ያላቸውን እምነት እና ድጋፍ እንዲቀጥሉ ባንኩ በአክብሮት ይጠይቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያየ መንገድ የባንኩን የውስጥ መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን በተዛባ መልኩ አሳልፈው የሚሰጡ እና የተቋሙን ሚስጥር በማይጠብቁ አንዳንድ የውስጥ አባላት ላይ ባንኩ በማስረጃ በማረጋገጥ የማያዳግም እርምጃ እስከሚወስድ ድረስ በዚህ አጋጣሚ ድርጊታቸው ባንኩን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑና በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ባንኩ በጥብቅ ያሳስባል።

በባንኩ ላይ ኃላፊነት በጎደለው እና ተጠያቂነት የሌለ እስኪመስል ድረስ መሰረት-ቢስ በሆነ እና ተቆርቋሪ በመምሰል ነገር ግን ከፋፋይ በሆነ መንገድ ባንኩን ብሎም ህዝብን የሚያውኩ የውጭ አካላትም ከዚህ ተግባራቸው እኩይ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ባንኩ አስጠንቅቋል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories