በኢትዮጵያ 2026 ኢንቨስት ያድርጉ ቢዝነስ ፎረም ” invest in Ethiopia 2026: High Level Business Forum” ሊካሄድ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን አስታወቀ

 “Invest in Ethiopia 2026፡ High Level Business Forum” ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላትን ዝግጁነት በስፋት እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አራተኛውን “Invest in Ethiopia 2026: High Level Business Forum” መጋቢት 17 እና 18 በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ነው ያስታወቀው፡፡

በፎረሙ ከሰባት መቶ በላይ የሚሆኑ ዓለም አቀፍ የቢዝነስ መሪዎች፣ ፖሊስ አውጪዎችና አጋር የልማት ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ቅዳሜ ገበያ  ኮሚሽኑ ካወጣው መግለጫ ተመልክታለች።

ፎረሙ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ለማዘመን እየተገበረች ያለውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ እንዲሁም ያሉትን አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ፤ አዲስ እና የማስፋፊያ የኢንቨስትመንት ቃልኪዳኖች እንዲገቡ አላማ አድርጎ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

በሀገሪቱ በኢንቨስትመንት መስክ የተለዩትን  የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ ፣ግብርና ፣ አይሲቲ፣ የማዕድን እና ታዳሽ ኃይል እንዲሁም የቱሪዝም እና አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን አማራጮች በዚህ ፎረም በስፋት ይተዋወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 በፎረሙ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን በግል ባለሀብቱ እና በመንግስት መካከል የፖሊሲና የኢንቨስትመንት ውይይት ይደረጋል እንዲሁም የአቻ ለአቻ ቢዝነስ ውይይቶች ፤ኢንቨስትመንት አማራጭ ኤግዚቢሽኖች እና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና  በኢንዱስትሪ ፓርኮች ጉብኝት እንደሚደረግ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories