የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ 84 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በ3ኛው የደረጃዎች ቦርድ በማስጸደቅ ወደ ተግባር ማስገባቱ ተጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ በቅርቡ ባካሄደው 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ውይይትና ምርመራ ካደረገ በኋላ ማፅደቁ የሚታው ሲሆን 68 አስገዳጅ ደረጃዎችን እና 16 የፍተሻ ዘዴ/ደረጃዎችን በድምሩ 84 አዲስ ደረጃዎች በማስጸደቅ ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል::
የጸደቁት ደረጃዎች በሦስት ዘርፎች የተለዩ ሲሆን በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ብዛታቸው 9 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣ለዚሁ ለፈጥሮ ጋዝ ምርቶች የሚያገለግሉ 11 የፍተሻ ደረጃዎች ጋይድላይን፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ የተፈጥሮ ጋዝ መሰረተ ልማት ደረጃዎች ብዛታቸው 23 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣የኃይል ፋክተር ማስተካከያ ብዛታቸው 7 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች፣ በዚሁ ዘርፍ ስር 5 የፍተሻ ደረጃዎች፣ የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች የማቀዝቀዣ/ፍሪጅ 1 አዲስ አስገዳጅ ደረጃ፣ በኮንስትራክሽን እና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ፣ የብረት እና አልሙኒየም ብዛታቸው 28 የሆኑ አስገዳጅ ደረጃዎች እንደሆኑታውቋል፡፡
ደረጃዎቹ ወቅታዊ የሀገሪቱን ፖሊሲ መነሻ አድርገው የተዘጋጁ እንደሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በተለይ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚታመነው የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ገበያው በሚገባበት ጊዜ ደረጃዎቹን በመተግበር በተገቢው መንገድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ እና ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡@seco


