የዓለማችን ቀዳሚ የኮባልት አምራች የሆነችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ የማዕድኑ አቅርቦት በመጨመሩና ዋጋው በመቀነሱ ምክንያት ላለፉት አሥር ወራት አቋርጣው የነበረውን የኮባልት ኤክስፖርት ዳግም መጀመሯን አስታውቃለች።
የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዱዱ ፍዋምባ እንዳሉት ኮንጎ ከዓለም የኮባልት ፍላጎት ከ70 በመቶ በላይ የምታቀርብ ቢሆንም፣ በገበያው ላይ የዋጋ መወሰን አቅም ማጣቷ ተገቢ እንዳልሆነና ምርቱን ማቋረጧም በዚሁ ምክንያት እንደነበር ገልጸዋል።
ለስማርት ስልኮችና ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ ምርት ወሳኝ ግብዓት የሆነውን ይህንን ማዕድን በሚመለከት፣ ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2024 ብቻ ከዓለም አጠቃላይ ምርት 76 በመቶ የሚሆነውን ማቅረቧን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።@seco


