የኢትዮጵያ ተደጋጋሚ የወደብ ልማት ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።
ወደ ጅቡቲ የወረዱት የግብፅ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ/ጀነራል ከማል ኤል ዋዚር እንደተጠበቀው ለወደብ ልማት ስምምነት አስረዋል።
ሁለቱ አገራት በ3 ጉዳይ ላይ ስምምነት ማድረጋቸው ነው የታወቀው።
ከስምምነቱ መካከል የግብፁ ኤልስዌዴ ኤሌክትሪክ በዶራሌ የኮንቴነር ወደብ 23 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የፀሃይ ሃይል መሰረተልማት መገንባት የሚያስችል፤
እንዲሁም የግብፅ ጭነቶችን ማስተናገጃ 10 ሄክታር መሬት በጅቡቲ አለምአቀፍ ነፃ ንግድ ቀጠና መስጠትን ያካትታል።
በተጨማሪ በጅቡቲ ግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በግብፁ የመንግስት ኩባንያ ሆልዲንግ ካምፓኒ ፎር ማሪታይም እና የብስ ትራንስፖርት መካከል የተደረ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትም የተካተተበት ነው።
በስምምነቱ መሰረት 5 ሚሊየን ኮንቴነር ማስተናገድ የሚችል አዲስ የኮንቴነር ወደብ ለመገንባት በመርህ ደረጃ ስምምነት ተደርሷል።
የት አካባቢ እና መቼ ወደቡ ይገነባል የሚለው ግን አልተገለፀም።
ኢትዮጵያ በወደብ ልማት ከጅቡቲ ጋር ለመስራት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ አንስቶ ፍላጎቷን ስትገልፅ ብትቆይም የተጨበተ ነገር አልታየም።
ባንፃሩ ሌሎች አገራት በጅቡቲ የሎጅስቲክ መሰረተልማት በጋራ ሆነ በተናጠል እንዲሁም ለበርካታ አመታት የማስተዳደር ስምምነት ሲያደርጉ እየተስተዋለ ነው።@seco


