ሸበሌ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 6 ቢሊየን ብር ተሻገረ

መሰረቱን ጅግጅጋ ከተማ ያደረገው ሸበሌ ባንክ 4ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ሀብቱ 6 ቢሊየን ብር  መሻገሩን አስታውቋል።

በኢንቨስትመንት ረገድ የታየው ዕድገት፣ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት እና በማህበራዊ ልማት ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸው በጉባኤው ተገልጿል።

አሁን ላይ ሸበሌ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ 6.03 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የደንበኞች ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 2.27 ቢሊዮን ብር መሆኑን አስታውቋል።

ባንኩ የሰጠው ጠቅላላ ኢንቨስትመንት መጠን 1.73 ቢሊዮን  ብር የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ገቢው ደግሞ 570.3 ሚሊዮን ብር ሆኗል፡፡

እናም ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት የ65.6% ዕድገት በማሳየት የተከፈለ ካፒታል መጠኑን 2.26 ቢሊዮን  አድርሷል።

ሸበሌ ባንክ በ65  ቅርንጫፎቹ በኢንቨስትመንት እና በዲጂታል ከእስልምና የሸሪዓ መርሆዎች ጋር የተጣጣሙ አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑንም አስታውቋል።

የሸበሌ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢና የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን “የባንኩ ስኬት ግልጽነት ላለው አሰራር፣ ለሕግና ደንብ ተገዢነት እንዲሁም ለዘላቂ ዕድገት ቁርጠኛ በመሆኑ የተገኘ ነው” ብለዋል፡፡

የባንኩ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱልጁሃድ ሀሰን መሐመድ “ባንኩ እያሳየ ያለው ዕድገት፣ ደንበኞች አስተማማኝ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ዕድገት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው” ብለዋል።@seco

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories