በኑሮ ውድነት ምክንያት በተነሳ ተቃውሞ ኢራን በተቃውሞ እየተናጠች ነው
በተካሄዱ ሰልፎች የሰው ህይወት መጥፋቱም ተዘግቧል፡፡
በመላው ኢራን የኑሮ ውድነትን በመቃወም ቢያንስ 6 ተቃዋሚዎች እና የጸጥታ ሃይሎች አባል እንደሞቱ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እያሳዩ ነው።
በኢራን፤ የገንዘብ የመግዛት አቅም መውደቅን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ የደቡባዊ ፋርስ ግዛት ነዋሪዎች የአካባቢውን አስተዳደር ሕንጻ ሰብረው ለመግባት ሞከረዋል።
በምዕራባዊ የሀሜዳን እና የሎሬስታን ግዛቶችም ተመሳሳይ ግጭቶች እንደተከሰቱ ተገልጿል።
እሁድ ዕለት በዋና ከተማዋ ቴህራን ተቃውሞ የተጀመረው በተቆጡ ነጋዴዎች ሲሆን ነጋዴዎቹ የኢራን ገንዘብ ከአሜሪካ ዶላር አንፃር በድጋሚ በከፍተኛ ሁኔታ መውደቁን ተከትሎ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።@SECO


