የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በእጅ (ማኑዋል) ይሰጥ የነበረው የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ በኦንላይን እንዲከናወን ተደርጓል።
ይህ አዲስ የዲጂታል አሰራር ላኪዎች ባሉበት ሆነው ያለ ምንም እንግልት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ለዜጎች እኩል ዕድል በመፍጠርና መተማመንን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
ይህ ማሻሻያ በተለይም እመርታ እያሳየ የመጣውን የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ይበልጥ ለማቀላጠፍና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ማንሰራራት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።@SECO


