የየመኑ ተገንጣይ መሪ አይዳሩስ አልዙበይዲ በሶማሊላንድ በኩል ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መኮብለላቸው ተገለጸ

በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የጥምረት ኃይል የየመኑ ደቡብ ሽግግር ምክር ቤት (STC) መሪ አይዳሩስ አልዙበይዲ በሪያድ ሊደረግ የነበረውን የሰላም ንግግር በማቋረጥ በሶማሊላንድ በኩል ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መኮብለላቸውን አስታወቀ።

ጥምረቱ  ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ አልዙበይዲ ረቡዕ ዕለት በሌሊት ከኤደን ተነስተው በጀልባ ወደ ሶማሊላንዷ በርበራ ወደብ ከተጓዙ በኋላ፣ ከዚያም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መኮንኖች ታጅበው በረራ አድርገዋል።

 አውሮፕላኑ ወደ አቡ ዳቢ በሚያቀናበት ወቅት የመለያ ምልክቱን አጥፍቶ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ክስተት በየመን ጉዳይ ላይ በሳዑዲ አረቢያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።

ይህንን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የየመን ፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት መሪ ራሻድ አል-አሊሚ፣ አልዙበይዲ “ከፍተኛ የሀገር ክህደት” ፈጽመዋል በሚል ከምክር ቤቱ ማሰናበታቸውንና በሕግ እንዲጠየቁ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የሳዑዲ ጥምረት በአልዙበይዲ ታማኝ ኃይሎች ላይ የአየር ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን፣ የየመን መንግሥት የምድር ጦር ደግሞ በኤደን የሚገኘውን ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት መቆጣጠሩ ታውቋል።

ምንም እንኳን አልዙበይዲ ቀደም ሲል በሳዑዲ አረቢያ በሚዘጋጀው የሰላም ንግግር ላይ እንደሚገኙ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ በሪያድ ሊታሰሩ ይችላሉ በሚል ስጋት ማምለጣቸው እየተነገረ ይገኛል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories