ዳንጎቴ ግሩፕ ከህንድ ኢንጂነሪንግ ኢንዲያ ሊሚትድ (EIL) ጋር በሌጎስ የሚገኘውን ዋና ማጣሪያ እና ፔትሮኬሚካል ለማስፋፋት የ350 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ስምምነት አድርጓል።
የማስፋፊያ ግንባታው የነዳጅ ማጣሪያውን አቅም በቀን ከ650,000 ወደ 1.4 ሚሊዮን በርሜል ያሳድገዋል፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ትልቅ ባለ አንድ ቦታ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ተርታ እንዲመደብ ያደርገዋል።
በሌኪ ፍሪ ዞን የሚገኘው የዳንጎቴ ማጣሪያ ናይጄሪያ ከነዳጅ ማስመጣት ጥገኝነት ወደ የተጣራ የነዳጅ ምርቶች አምራች እና ላኪነት መሸጋገሯን ያሳያል። ፕሮጀክቱ የፔትሮኬሚካል ምርትን ያሳድጋል ተብሏል፡፡@SECO


