የትራምፕ አዲስ የታሪፍ ዛቻ በዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግሪንላንድን ለመግዛት የሚያደርጉትን ጥረት ተከትሎ በስምንት የአውሮፓ አገራት ላይ የጣሉት አዲስ የታሪፍ ማስፈራሪያ፣ የነገ ሰኞ የገበያ ውሎ ከመጀመሩ በፊት በዓለም አቀፍ የአክሲዮን ገበያዎች ላይ ስጋት አንዣቧል።

ትራምፕ ከየካቲት 1 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የ10 በመቶ ታሪፍ፣ በኋላም ሰኔ 1 ቀን ወደ 25 በመቶ ከፍ የሚል ቀረጥ በመጣላቸው፣ የአውሮፓና የአሜሪካ የንግድ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ገብቷል።

የገበያ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የነገው የሰኞ ገበያ ሲከፈት የለንደን አክሲዮን ገበያ የ0.9 በመቶ፣ የአሜሪካው ዳው ጆንስ ደግሞ የ0.5 በመቶ ቅናሽ ሊያሳዩ እንደሚችሉ ምልክቶች ታይተዋል።

 በተቃራኒው፣ የጂኦፖለቲካ ውጥረቱ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን ወደ ዋስትና ወዳላቸው ንብረቶች እንዲያሸሹ በማድረጉ፣ የወርቅ ዋጋ በ0.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ በአንድ አውንስ 4,625 ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፈው ሳምንት ተመዝግቦ ከነበረው ከፍተኛው የ4,642 ዶላር ታሪካዊ ዋጋ ጋር እንዲቀራረብ አድርጎታል።

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመርና የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ውሳኔውን አጥብቀው ተችተዋል።

የብሪታንያ ንግድ ምክር ቤቶች  ባወጣው መግለጫ፣ አዲሱ ታሪፍ ለብሪታንያ ላኪዎች “ሌላ መጥፎ ዜና” መሆኑን ገልጾ፣ መንግሥት ከዋይት ሀውስ ጋር በሰላማዊ መንገድ እንዲደራደር አሳስቧል።

የጀርመን የመኪና አምራቾች ማህበር በበኩሉ፣ የታሪፉ ዋጋ ለአውሮፓ ኢንዱስትሪዎች “እጅግ ከፍተኛ” እንደሚሆንና ሸክሙም ወደ አሜሪካውያን ሸማቾች ሊዞር እንደሚችል አስጠንቅቋል።

አንዳንድ የአውሮፓ የንግድ ማህበራት ኅብረቱ “የአጸፋ መሣሪያውን” በአሜሪካ ላይ እንዲጠቀም ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።

“ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት እጅ ከሰጠን፣ ሌሎች የማይረቡ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብና ተጨማሪ ታሪፎችን እንዲጥል መንገድ መክፈት ነው” ሲሉ የጀርመን መሃንዲሶች ማህበር ፕሬዝዳንት ቤርትራም ካውላት በቁጭት ተናግረዋል። የነገው የሰኞ ገበያ ውሎ የትራምፕ የታሪፍ ዛቻ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን እውነተኛ ተፅዕኖ በግልጽ እንደሚያሳይ ይጠበቃል።@SEECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories