የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ሀገራቸው በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ከቻይናም ሆነ ከሌላ ከማንኛውም ሀገር ገንዘብ እንደማትበደርና በውጭ ብድር ላይ ያለባትን ጥገኝነት እንደምታቆም አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ በኬንያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ባላቸው የኢኮኖሚ ነፃነትና ዘላቂ እድገት ራዕይ ዙሪያ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ ከውጭ ብድር ይልቅ የአገር ውስጥ ቁጠባን ለልማት ስራዎች በማዋል የራሷን የፋይናንስ ሉዓላዊነት የምታጠናክር ይሆናል።
ይህ ስትራቴጂ ተግባራዊ ከሆነ የኬንያን ኢኮኖሚ ከማረጋጋቱም በላይ ዜጎች በአገር ግንባታ ላይ ንቁ ሚና እንዲጫወቱና በራስ የመተማመን አቅም እንዲገነቡ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።@SECOO


