በአኩሪ አተር የውሸት ቡና ሲያመርት የነበረ ድርጅት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ

የቬትናም ፖሊስ በአኩሪ አተር እና በተለያዩ የጣዕም ማቀናበሪያ ኬሚካሎች የውሸት ቡና ሲያመርት የነበረን አንድ መጋዘን በወንጀል ምርመራ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በሀገሪቱ የቡና ምርት ማዕከል በሆነችው ላም ዶንግ ግዛት ውስጥ በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻ፣ ፖሊስ 4.1 ቶን የተዘጋጀ የውሸት ቡና እና 3 ቶን ጥሬ እቃዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

 ለዚህ ምርመራ መነሻ የሆነው ባለፈው ማክሰኞ ፖሊስ አንድን ተሳቢ መኪና አስቁሞ በፈተሸበት ወቅት ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ የሌለው 528 ኪሎ ግራም የተፈጨ ቡና በማግኘቱ ሲሆን፣ የምርመራው ሂደት ሲሰፋም የመጋዘኑ ባለቤት አኩሪ አተርን ከኬሚካሎች ጋር በመቀላቀል ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚቀርብ ቡና ሲያመርቱ እንደነበር ተረጋግጧል።

ይህ የማጭበርበር ድርጊት የተስፋፋው በቬትናም የቡና ዋጋ ከአኩሪ አተር በሶስት እጥፍ በመብለጡ እንደሆነ ተገልጿል። ምንም እንኳን አኩሪ አተር ለምግብነት የሚውል ቢሆንም፣ ቡና ለማስመስል የሚጨመሩት ኬሚካሎች ለጤና ያላቸው ደህንነት አለመታወቁ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

 ቬትናም የአለም ትልቁ የሮቡስታ ቡና አምራች በመሆኗ እና ባለፈው አመት ብቻ 8.9 ቢሊዮን ዶላር ከዘርፉ በማግኘቷ፣ እንዲህ ያሉ የሐሰት ምርቶች የሀገሪቱን የንግድ ስም ሊያበላሹ እንደሚችሉ ተሰግቷል።

 ፖሊስ በ2018ም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው የተገኙ ግለሰቦችን ማሰሩን በማስታወስ፣ አሁንም በሌሎች አካባቢዎች መሰል ወንጀሎች እንዳይኖሩ ጥብቅ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories