አየር መንገዱን በከፊል ወደ ግል የማዛወር ወይም አክሲዮኖችን ለሕዝብ ክፍት የማድረግ  እቅድ እንደሌለ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አክሲዮኖቹን ለሕዝብ ክፍት የማድረግ (IPO) ወይም ተቋሙን በከፊል ወደ ግል የማዛወር ዕቅድ እንደሌለው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ገለጹ።

ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰዉ እንደገለፁት፣ ምንም እንኳ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉ ተቋማት ወደ IPO እየገቡ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን አሁንም መቶ በመቶ በመንግሥት የተያዘ ድርጅት ሆኖ ይቀጥላል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ከቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታና ከአውሮፕላን ግዢ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ብድር ከውጭ አገራት እንደሚያገኝ የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚው፣ በአገር ውስጥ አፋጣኝ የሆነ የካፒታል ፍላጎት ስለሌለ ወደ አክሲዮን ሽያጭ መግባት አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም ብለዋል።

አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። ለዚህ ከፍተኛ የገቢ ዕድገት ዋነኛው ምክንያት የኦፕሬሽን ስራዎችን ማስፋፋት መሆኑ ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል አዳዲስ የበረራ መስመሮችን መክፈት፤ ነባር የበረራ መስመሮች ላይ የጉዞ ድግግሞሽን (Frequency) መጨመር፤ ለምሳሌ ወደ ሌጎስና አቡጃ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች በቀን ከአንድ ወደ ሁለት ከፍ እንዲሉ በመደረጉ መሆኑን ቅዳሜ ገበያ ሰምታለች።

የአገር ውስጥ የበረራ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ፣ አየር መንገዱ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት የጥናትና የድርድር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት የ Q400 አውሮፕላኖች ምርታቸው በመቆሙ፣ አየር መንገዱ እነዚህን የሚተኩ አዳዲስ የ “ጀት” አውሮፕላኖችን ለመግዛት የገበያ ጥናት (Evaluation) እያደረገ እንደሚገኝ ቅዳሜ ገበያ ለመረዳት ችላለች።

ለረጅም ርቀት መንገደኞችና ለጭነት አገልግሎት የሚውሉ ትላልቅ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከአምራቾች ጋር የዋጋ ድርድር እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

አየር መንገዱ በቅርቡ በሪጅናል ጀትና በትላልቅ አውሮፕላኖች ግዢ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories