ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ በተጨማሪ መርከብ ግዥዎች ላይ ለውጥ አደረገ

በኢቢቪ ዘጋቢ

ግዙፉ የመርከብ አንቀሳቃሽ መንግስታዊ ኩባንያ፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) ሊገዛቸው ባሰባቸው ተጨማሪ መርከቦች ላይ የፍላጎት መጠይቅ ማሻሻያ አደረገ፡፡

ተቋሙ ከፍ ያለ የመጫን አቅም ያላቸው በመካከለኛ ደረጃ የሚጠቀሱ አልትራ ማክስ እና ኮንቴነር ጫኝ መርከበችን ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው ሲገልፅ መቆየቱ  የሚታወሰን ነው፡፡

ለግዥ ሂደቱም ቀደም ሲል ጨረታ አውጥቶ የነበረ ቢሆንም አሁን በድጋሚ ሌላ ጨረታ መውጣቱ ነው በዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አብዱልበር ሸምሱ የተገለጸው፡፡

ከመርከብ ግዥው መካከል 4 ያገለገሉ መርከቦች የሚገኙበት እንደመሆኑ የስራ አመራር ቦርድ በግዥ ሂደቱ ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው እና የግዥ ሂደቱ በደላላ አማካኝነት እንዲደረግ ቦርድ በመቀበሉ ጨረታው በድጋሚ ሊወጣ እንደቻለ ነው ሃላፊው ለኢትዮጵያን ቢዝነስ ቪው (ኢቢቪ) ዘጋቢ የገለፁት፡፡

‹‹ያገለገሉ መርከብ ግዥዎች የሚከናወነው በመርከብ ደላሎች አማካኝነት ነው፣›› ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ‹‹የጨረታ ሂደቱ በደላላ መረጣ እንዲጀመር ለቦርድ በማስረዳት በዛ መልኩ ቦርዱ ይሁንታ ሰጥቶ ጨረታ ወጥቷል፣›› ሲሉ አክለዋል፡፡

አዲሱን የጨረታ ሰነድ ኢቢቪ እንደተመለከተው ከሆነ በጨረታ ለመግዛት የታቀደው መርከብ ላይ ለውጥ ተደርጓል፡፡

ቀደም ሲል ወጥቶ በነበረው ጨረታ ተቋሙ እስከ 65 ሺ ቶን ጠቅላላ የጭነት  አቅም ያላቸው ሁለት ያገለገሉ ብትን ጭነት የሚይዙ/ bulk carriers አልትራ ማክስ መርከቦች፣ ከ 3  እስከ 5 ሺ 20 ጫማ ኮንቴነር መጫን የሚችሉ መካከለኛ ሁለት ያገለገሉ እንዲሁም አዳዲስ ሁለት ሁለገብ ጭነት የሚይዙ አልትራ ማክስ መርከቦቸችን ለመግዛት ታቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም በአዲሱ ጨረታ ኢባትሎ የቀደመ እቅዱን በመቀየር ብትን ጭነት የሚይዙ አልትራ ማክስ መርከቦች ብዛት ወደ 3 ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡ በዚህም ኩባንያው የኮንቴነር ጫኝ መርከብ ግዝውን ከ ሁለት ወደ አንድ ዝቅ ማድረጉ ነው የጨረታ ሰነዱ የሚያሳየው፡፡

አዳዲሶች እስከ 65 ሺ ቶን ሸክም መያዝ የሚችሉ መርከቦች በግንባታ የሞገዙ ሲሆን ለመከርብ አንቀሳቃሹ በአልትራ ማክስ ደረጃ ያሉ የመጀመሪያ ሁለገብ ጭነት የሚይዙ መርከቦች ይሆናሉ፡፡

አሁን ላይ ኢባትሎ ዝቅተኛ የመጫን አቅም ያላቸው ሃንዲ ሳይዝ መርከቦችን ነው ለሁለገብ ጭነት የሚጠቀመው በመሆኑም የአልትራ ማክሶቹ መምጣት የመጫን አቅማቸው በመካከለኛ ደረጃ የሚገኝ በመሆኑ የማጓጓዝ አቅሙን የሚያጎለብቱ ናቸው፡፡

በአዲሱ የግዥ ሂደት እንዲሁ የገንዘብ አቅርቦት ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ነው የተገለጸው፡፡ በቀደመው እቅድ ኢባትሎ ከዳሽን፣ አዋሽ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የፋናንስ አቅርቦት እንዲኖር ሲደራደር ነበር፡፡

በእቀዱ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ አዲስ አልትራ ማክስ መርከብ እና ሁለት ኮንቴነር መርከቦችን በመግዛት ሂደት ፋይናንስ ሊያደርግ እንዲሁም ዳሽን እና አዋሽ ባንኮች  አንድ ያገለገለ እንዲሁም አንድ አዲስ መርከቦችን በፋይናንስ ለመደገፍ ታስቦ የነበረ ሲሆን፡፡ የብድር አቅርቦቱም 70 በመቶ ከባንኮቹ ቀሪው በኢባትሎ የሚሸፈን እንዲሆን ነበር፡፡ በተጨማሪ አንደኛውን መርከብ እራሱ እባትሎ ወጪውን በሙሉ ሸፍኖ ለመግዛት ነበር እቅዱ፡፡

ሆኖም አቶ አብዱልበር እንደተናገሩት በአዲሱ እቅድ ንግድ ባንክ ለሁሉም ስድስት መርከቦች ግዥ 50 በመቶ ሊሰጥ እንዲሁም ቀሪውን 50 በመቶ ኢባትሎ እንዲሸፍን ድርድር እየተደረገ ነው፡፡

አሁን ላይ ኢባትሎ አባይ ሁለት የተሰኘች አንድ ብትን ጭነት የሚትይዝ እንዲሁም የመያዝ አቅማቸው 28 ሺ ቶን የሆነ ሃንዲ ሳይዝ የሚባሉ ሁለገብ ጭነት የሚያጓጉዙ 9 መርከቦች አሉት፡፡

በአፍሪካ ብቸኛ አህጉር አቋራጭ/deep sea መርከቦች አንቀሳቃሽ እንደሆነ የሚገለፀው ኩባንያው እስከ 2022 16 መርከቦችን ለመግዛት አቅዶ እየሰራ ነው፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories