የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው የማዳበሪያ መሸጫ ዋጋን ለመወሰን በመዘግየቱ ምክንያት፣ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በወቅቱ ለመዝራት መቸገራቸውና ይህም በበልግ ወቅት በሚገኘው ምርት ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋት ተፈጠረ።
የማዕከላዊ ባንክ ገዥን እና የገንዘብ ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን በአባልነት የያዘው የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ፣ ከየካቲት እስከ ሚያዝያ ለሚዘልቀው የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች አርሶ አደሩ ማዳበሪያውን የሚገዛበትን የዋጋ ተመን እስካሁን አላሳወቀም።
የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሰባት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለፓርላማው የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ባለፈው ዓመት ተገዝቶ ያልተሰራጨ 4 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መጋዘኖች ውስጥ ይገኛል።
ይሁን እንጂ የዋጋ ተመኑ ባለመወሰኑ ማዳበሪያው ወደ አርሶ አደሩ ሊሰራጭ አልቻለም። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ እንደተናገሩት፣ ማዳበሪያው በመጋዘን ተከማችቶ እያለ በዋጋ ውሳኔ መዘግየት ምክንያት ለአርሶ አደሩ አለመድረሱ በበልግ ወቅት የሚመረቱ እንደ ስንዴ እና ገብስ ያሉ አጫጭር የሰብል ዓይነቶች ላይ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።
እንደ ሪፖርተር ዘገባ፤ ይህ በዋጋ ውሳኔ ላይ የታየው መዘግየት በአርሶ አደሩ ዘንድ ትልቅ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን፣ መንግስት ለአቅርቦቱ ትኩረት ሰጥቶ ፈጣን ውሳኔ ካላሳለፈ የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ጥረት ሊያደናቅፍ እንደሚችል ተጠቁሟል።@SECO


