የአፍሪካ ልማት ባንክ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡን አስታወቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ  ፕሬዝዳንት ሲዲ ኦልድ ታህ እንደገለጹት ባንኩ አነስተኛ ገቢ ላላቸው የአፍሪካ አገራት ድጋፍ የሚውል 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡን ይፋ አድርገዋል።

ይህ በታሪክ ከፍተኛ የተባለው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት፣ አፍሪካ በውጭ ዕርዳታ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስና “New African Financial Architecture (NAFA)” በተሰኘው አዲስ ስትራቴጂ አማካኝነት የራሷን የውስጥ ሃብት በመጠቀም የፋይናንስ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለጀመረችው ጉዞ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ትኩረታቸው የወጣቱን የሰው ሃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ፀጋ መቀየር፣ የተፈጥሮ ሃብትን እሴት መጨመር እና በአህጉሪቱ ያለውን የፋይናንስ ክፍተት መሙላት ላይ እንደሚሆን ገልጸዋል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories