በዳሸን ባንክ “ዱቤ አለ”

ዳሸን ባንክ ዘመናዊ የዱቤ ግብይትን ባስተዋወቀበት የ”ዱቤ አለ” አገልግሎት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ አበደረ

ዳሸን ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት አቅራቢ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ባቀረበዉና ዘመናዊ የዱቤ ግብይትን ባስተዋወቀበት የ”ዱቤ አለ” አገልግሎት ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ አበደረ፡፡

ባንኩ ከጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ባስጀመረው በዚህ አገልግሎት ከ21,000 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ማቅረብ የቻሉ ሲሆን፣ ከ470,000 ሺህ በላይ የሆኑ ደንበኞች ደግሞ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

“ዱቤ አለ” ዳሸን ባንክ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ምርትና አገልግሎት የሚያቀርቡ የንግድ ድርጅቶች ጋር በጥምረት ያቀረበዉ በቴክኖሎጂ የታገዝ የዱቤ አሰራር ሲሆን፣ በመደበኛና የሸሪዐህ መርሆዎችን በተከተለ አሰራር በቀረበው በዚህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና በርካታ አገልግሎቶችን በ3 ወር፣ በ6 ወርና በ12 ወር በሚመለስ ዱቤ በወለድና ያለወለድ መግዛት የሚያስችል አማራጭ እንደሆነ ተነግሯል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories